የአንጎላው ፕሬዚደንት ሆዜ ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ የያዙት ሥልጣን በሚያበቃበት ዘመን ማለትም እ.አ.አ. በ2018 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ከፖለቲካው ዓለም እንደሚገለሉ አስታወቁ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ከአፍሪቃ የረዥም ጊዜ መሪዎች አንዱ የሆኑት የአንጎላው ፕሬዚደንት ሆዜ ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ የያዙት ሥልጣን በሚያበቃበት ዘመን ማለትም እ.አ.አ. በ2018 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ከፖለቲካው ዓለም እንደሚገለሉ አስታወቁ።
ፋይል ፎቶ - ዶስ ሳንቶስ
ዶስ ሳንቶስ ዛሬው ዕለት ለገዥው ኤምፒኤልኤ (MPLA) ፓርቲ አባላት ዋና ከተማዋ ሉዋንዳ ውስጥ ሲናገሩ፣ "ከ2018 በኋላ ምንም ዓይነት ንቁ የፖለቲካ ተሳትፎ አላደርግም" ማለታቸው ተደምጧል። ይህን የወሰኑበትን ሚክናት ግን አላብራሩም።