የኢትዮጵያ መንግሥት ሠላማዊ ሰልፍ ያለመፍቀዱን አምነስቲ ተቸ

ዜጎች ሰልፍ እንዳይወጡ መከልከል ሐሳብን በነፃነት የመግለፅና የመሰብሰብ ነፃነትን መጣስ ነው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ትችት አቅርቧል።

ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቋም ጉዳዩን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ የሚፈፀመው ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ለማውገዝ ለዛሬ የተጠራው ሰልፍ በመንግሥት መከልከሉን ተከትሎ የወጣ ነው።

የአማራ ክልል መንግሥት ግን ሰልፉ የተከለከለው ተጨባጭ በሆነ የፀጥታ ስጋት ነው ብሏል።

Your browser doesn’t support HTML5

“የአብን ሰልፍ የተከለከለው ተጨባጭ በሆነ የፀጥታ ስጋት ነው” - አቶ ግዛቸው ሙሉነህ

የክልሉ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል ላይ እምነት እንደሌላቸው ተናግረዋል።

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ በእምቢተኛነት ሰልፍ ባለማድረጉም አመስግነዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ መንግሥት ሠላማዊ ሰልፍ ያለመፍቀዱን አምነስቲ ተቸ