በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አብን የጠራው ሰልፍ ተሰረዘ


የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጣሂር መሐመድ
የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጣሂር መሐመድ

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ ፓርቲ ጥቅምት 18/2013 ዓ.ም በአማራ ብሄራዊ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ጠርቶን የነበረውን ሰልፍ መሰረዙን አስታወቀ።

የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጣሂር መሐመድ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ የተጠራውን ሰልፍ መምራት ስለማንችል ሰልፉ ተሰርዟል ብሏል።

አብን ዛሬ ጠዋት ስለሰልፉ ዝርዝር ጉዳዮች በቢሯቸው ውስጥ ሲወያዩ እና ከሰዓት በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት እየተዘጋጁ ባሉበት ሰዓት በአዲስ አበባ የፀጥታ ኃይል የፓርቲው ጽ/ቤት መከበቡን አቶ ጣሂር ገልፀዋል።

ስለጉዳዩ ከአዲስ አበባ ፖለሲ ለማጣራት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

አብን የጠራው ሰልፍ ተሰረዘ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:04 0:00


XS
SM
MD
LG