አፍሪቃ በጋዜጦች

ፋይል ፎቶ - ሁጂያን የጫማ ፋብሪካ በዱከም ኢትዮጵያ ውስጥ

አፍሪቃ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራምን ስለ አፍሪቃ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል። ዩናይትድ ስቴትስና ቻይና የኢትዮጵያን የግል ዘርፍ እያዳበሩ እንደሆነ ተዘገበ፣ ኢትዮጵያ ድርቁን ለመቋቋም አለም አቀፍ ረድኤት ያስፈጋታል ተባለ፣ ግብጽ ከምስራቅ አፍሪቃ የመብራት ሃይል ቅንጅት አባልነት መውጣትዋ ታወቀ የሚሉትን ርእሶች ነው በዛሬው ቅንብራችን የተመለከትነው።

የአፍሪቃ ሪፖርት (The Africa Report) የተባለው ስለ አፍሪቃ ዜና፣ ትንታኔና የአመለካከት ጽህፉፎች የሚያቀርበው መጽሄት ድረ-ገጽ The African Growth and Opportunity Act (AGOA) በተባለው የአፍሪቃ የእድገት እድል ውል መሰረት የዩናይትድ ስቴትስና የአፍሪቃ የንግድ ህግ በውሉ ለተካተቱት የአፍሪቃ ሀገሮች በዩናይትድ ስቴስ ገበያዎች ከቀረጥና ከጣርያ ነጻ የሆነ ተደራሽነት እንዲያገኙ ያደርጋል ይላል። ይህን መሰረት በማድረግ ታድያ ከኢትዮጵያ ወደ ዩናይትድ ስቴስ የሚላከው የጫማ ንግድ መጠን እንደመጠቀ ድሁፉ ጠቁሟል።

የዩይትድ ስቴስ አለም አቀፍ የልማት አገልግሎት (USAID ) አሃዝ በጠቆመው መሰረት ከኢትዮጵያ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የሚላከው ጫማ በ $630,000 ይገመት እንደነበር ከሶስትና ከአራት አመታት በፊት በነብረው ጊዜ ግን ወደ $7 ሚልዮን ዶላር እንደተጠጋ ዘገባው ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ የጫማ ኢንዱስትሪ ድሮም ቢሆን ጥራት ያለው የቆዳ ጫማ በማምረት ይታወቃል። አሁን ደግሞ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ያለ በመሆኑ፣ አስተማማኝ የኤለክትሪክ ሃይል ምንጭና ርካሽ ጉልበት በመኖሩ አለም አቀፍ ኩባንያዎችና አቅራቢዎች በጫማ ኢንዱስትሪ ለመጠቀም ወደ ኢትዮጵያ መጉረፋቸው አያስደንቅም ይላል የአፍሪቃ ሪፖርት ድረ-ገጽ ላይ የወጣው ጽሁፍ።

ኢትዮጵያ ከመላ አፍሪቃ የበዙ የቀንድ ከብት ሃብት አላት። በአለም ደረጃም ብዙ ከብት ካላቸው ሃገሮች አንዷ ናት። የኢትዮጵያ ኩባንያዎች እአአ ከ 1930ዎቹ አመታት አንስተው የቆዳ ምርት ወደ ውጭ ሲልኩ ቆይተዋል ሲል ዘገባው አውስቷል።

የብሪታንያ የዜና ስርጭት ኮርፐረሽን BBC ደግሞ ኢትዮጵያ ካለፉት 15 አመታት ወዲህ ከቱርክሜንስታን ጋር ከአለም በከፍተኛ ፍጥነት ስታድግ የቆየች ሀገር በመሆንዋ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከድህነት እንዲወጡ አድርጋለች።

የሀገሪቱ የእድገት ደረጃ በህንጻዎች ግንባታ ቦታዎችና በእያንዳንዱ የአዲስ አበባ ማእዝናት ባሉት ረዣዥም ፎቆች ይንጸባረቃል። ሃገሪቱ በ 30 አመታት ውስጥ በጣም ተቀይራለች። ከ 30 አመታት በፊት በደረሰው ከባድ ድርቅ ምክንያት በተከተለው ረሀብ በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አልቀዋል። ያ ትዝታ አሁንም ገና ብዙ የመስራት አላማ ላለው የውቅቱ መንግስት ያልደረቀ ቁስል ነው በማለት ዘገባው ያለፈውን ያስታውሳል።

አሁንም እንደገና ኤል ኒኖ ባስከተልው ድርቅ ምክንያት መሬቱን ወደ አቧራ ቀይሮታል። አሁንም እንደገና ከ 30 አመታት በፊት የታየውን ያህል አስከፊ ድርቅ ገጥሟታል። የአሁኑ ድርቅ ያኔ ከነበሩት የበዙ ቦታዎች ላይ ተዳርሷል። እንዳውም አንድ ሰውየ በ 45 አመታት ውስጥ ይህን አይነት አስከፊ ድርቅ አይቼ አላውቅም ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

ግብጽ ከምስራቅ አፍሪቃ የመብራት ሃይል ቅንጅት አባልነት መውጣትዋን በሚመለክትም አለን። ሙሉውን ቅንብር ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

አፍሪቃ-በጋዜጦች-2-12-16