ኢትዮጵያ እጅግ ምቹ ሊባል ከሚችል ቦታ ላይ ሆና ከዋክብትን እየተመለክተች ነው በሚል ርእስ የሲኤንኤን ድረ-ገጽ ባቀረበው ዘገባ ለኢትዮጵያ ወጣቶች ራእይ ጣራው ሰማይ ነው። አዲስ አበባ ላይ ባሉት ትምህርት ቤቶች የሚሰሙት የወጣቶች ምኞቶች በአለም ትምህርት ቤቶች ያሉትን ያህል ገደብ የላቸውም ሲል ገልጾታል።
የ 17 አመት እድሜ ወጣት የሆነችው ሜሮን መኮንን ከአቶሞች ያነሱ ንጥረ ነገሮችንና የጨረራ ፊዚክስ ሳይንቲስት መሆን ትፈልጋለች፣ ሌላው ወጣት የሮኬት ሳይንቲስት፣ ዳግም ተረሳ ደግሞ የሮቦት ስራ ኢንጂኔር መሆን ይፈልጋሉ።
ሜሮን መኮንን ኤንስታይን ስለ ሬላቲቪቲ ንድፈ ሀሳብ ሲጽፍ ገና ወጣት ነው የነበረው። የሱ አንድ ጥቅስ ነው የሳይንስን ታሪክ የለወጠው። እኔም ብዙ ሃሳቦች አሉኝ ስትል የአፍላቂነት ምኞትዋን እንደገለጸች የሲኤንኤን ድረ-ገጽ ገጽ ላይ የወጣው ዘገባ ጠቅሷል።
የወቅቱ ወጣቶች ወደ ከዋክብት ለመድረስ እንዲጣጣሩ ሁሌም ይበረታታሉ። አንዳንድ የኢትዮጵያ ወጣቶች ግን በሀገሪቱ ለመጀመርያ ጊዜ በተመሰረተው የጠፈር ፕሮግራም ምክንያት በከዋክብት የመድረስ ምኞታቸው እውን ሊሆን እንደሚችል ዘገባው ያወሳል።
የኢትዮጵያ የጠፈር ሳይንስ ማህበር ቦርድ ሊቀመንበር ከላሊ ተክሌ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ሳተላይት የመስራት አቅም ባይኖራትም ከሌሎች ተቋማት ጋር እየሰራን ነው። የኛ ኢንጂኔሮች ተመክሮ እንዲያገኙ ይሳተፉሉ። በሶስትና አምስት አመታት ውስጥ መሬትን የምንመለከትበትና የምናጠናበት ሳተላይት ይኖረናል” ማለታቸውን የሲኤንኤን ድረ-ገጽ አስነብቧል።
የቢቢሲ ማለት የብሪታንያ የዜና ስርጭት ኮርፐረሽን ድረገጽ ደግሞ የአፍሪቃ ፈጥኖ ደራሽ ሰራዊት ከተጠነሰስ 13 አመታት በኋላ እውን ሊሆን ነው በሚል ርእስ ባወጣው ጽሁፍ ከመጪው ጥር ወር አንስቶ አንዲት የአፍሪቃ ህብረት አባል ሀገር ከጠየቀች የጦርነት ወንጀል ፍጅት ወይም በስብእና ላይ ወንጀል ቢፈጸም ወይም ደግሞ የአፍሪቃ ህብረት ራሱ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው የአፍሪቃው ተጠባባቂ ሃይል ጣልቃ ይገባል ይላል።
ሰብአዊ ረድኤት በማቅረብና በሰላም ጥበቃ እንዲሁም በታዛቢነት ተልእኮም ያገለግላል። ዘረፈ-ብዙ የሆነ ተልእኮ ያለው ወታደራዊ ሀይል አምስት ብሪጌዶች አሉት። በ 14 ቀናት ውስጥ በአከባቢው ሊመደቡ የሚችሉ የፖሊስ፣ ወታደራዊና ሲቪል ክፍሎች ይኖሩታል። የአፍሪቃ ደራሽ ሃይል ወታደራዊ እቃዎች ወይም ሎጂስቲክስ የሚቀመጠው ዳውላ በተባለችው የካሜሩን ከተማ ይሆናል። ዋናው ሃይል ግን የአፍሪቃ ህብረት ዋና ጽህፈት ቤት በሚገኝበት አዲስ አባባ ላይ ይሆናል።
ሙሉውን ዝግጅት ያድምጡ