ኢትዮጵያ ቀጥተኛ የባህር መውጫ እንዲኖራት በማሰብ መንግሥቷ ከሶማሊላንድ ጋር የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙን እንደሚደግፉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታውቀዋል።
ኢዜማ እና ኢሶዴፓ ሃገሪቱ የባሕር በር እንዲኖራት ማስቻል የፕሮግራማቸው አካል መሆኑን ገልፀዋል።
ስምምነቱ ለክልላቸው የተለየ ጥቅም ሊያስገኝ እንደሚችል የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ሙስጠፌ መሀመድ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ስምምነቱ እንደሚያሳስባቸው ያሳወቁ ኢትዮጵያዊ አካላትም መኖራቸው ይታወቃል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡