የዐማራ ክልል የአፈር ማዳበሪያ በአፋጣኝ ለአርሶ አደሩ ለማድረስ የትብብር ጥሪ አቀረበ

Your browser doesn’t support HTML5

የዐማራ ክልል የአፈር ማዳበሪያ በአፋጣኝ ለአርሶ አደሩ ለማድረስ የትብብር ጥሪ አቀረበ

በዐማራ ክልል ሰሞኑን በተስፋፋው ግጭት ሳቢያ፣ የ130ሺሕ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ሥርጭት መስተጓጎሉን የገለጸው የክልሉ ግብርና ቢሮ፣ በአፋጣኝ ወደ አርሶ አደሩ ለማድረስ ይቻል ዘንድ የትብብር ጥሪ አቀረበ፡፡

SEE ALSO: የአፈር ማዳበሪያ ጥያቄያቸው ያልተመለሰላቸው የዐማራ ክልል አርሶ አደሮች ስጋት አይሏል

የግብርና ቢሮው ምክትል ሓላፊ አቶ አበጀ ስንሻው፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በመጪው 10 ቀናት ውስጥ፣ ወደ ክልሉ የገባው 130ሺሕ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ፣ ወደ የአርሶ አደሩ ቀዬ ተጓጉዞ ካልደረሰ፣ በቀጣዩ ዓመት ረኀብ ሊከሠት ይችላል፡፡ ያነጋገርናቸው አርሶ አደሮች በበኩላቸው፣ አቅርቦቱ እጅግ ዘግይቷል፤ ብለዋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።