መንግሥት ድረ-ገፆችን መዝጋቱን በይፋ ሲናገር የመጀመሪያው ነው

  • እስክንድር ፍሬው

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምሕርት መግቢያ ፈተና መንግሥት የማኅበራዊ መገናኛ ድረ ገፆችን ከዘጋ በኋላ ተጀምሯል። እየተናፈሱ ያሉ ውዥንብሮችን ለመግታት ሲባል የማኅበራዊ ድረ-ገፆች እንዲዘጉ መወሰኑን መንግሥት አስታውቋል። እርምጃው በተጠቃሚው ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል። አንዳንድ ተማሪዎች ግን በአዎንታዊ ጎኑ ተመልክተውታል።