ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ፣ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የደራ ወረዳ ነዋሪዎች፣ ሸኔ እና ፋኖ ሲሉ በጠሯቸው ታጣቂዎች፣ ጥቃት እየደረሰባቸው እንደኾነ ገለጹ።
የወረዳው አስተዳዳሪ፣ በነዋሪዎቹ የቀረቡት ቅሬታዎች ትክክለኛ እንደኾኑ ገልጸው፣ በታጣቂዎቹ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ፣ ከክልሉ እና ከፌዴራሉ መንግሥት ድጋፍ እየጠየቁ እንደኾነ አመልክተዋል። የታጣቂዎቹ አባላት፣ በነዋሪዎቹ እና በአካባቢው ባለሥልጣናት የቀረበባቸውን ቅሬታ አስተባብለዋል፡፡ ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም