በአባታቸው ስም ተርታ ፣በአያታቸው ስም ምትክ እንዲያም ካልሆነ ደግሞ በመጠሪያቸው መጨረሻ በቅንፍ ውስጥ የእናታቸውን ስም የሚያካትቱ የኪነጥበብ ሰዎች እየበዙ ነው፡፡ ከእነዚህ መካከል ፡-ወጣቱ የሙዚቃ ሰው እሱባለው ይታየው የሺ ፣ደራሲ እና የባህል እና ትውፊት ተመራማሪው አንዱ ዓለም አባተ የአጸደ ልጅ እንዲሁም ዕውቁ ውዝዋዜ ባለሙያው አብዮት ካሳነሽ ይጠቀሳሉ፡፡
የፊታችን እሁድ የሚከበረውን “የእናቶች ቀን” ምክንያት በማድረግ፣ ባልደረባችን ሀብታሙ ስዩም የእናቶቻቸውን ስም ለየት ባለ መልኩ በሙሉ ስማቸው ውስጥ ከአካተቱ ሦስት ታዋቂ የኪነጥበብ ሰዎች ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ