ADDIS ABABA,ETHIOPIA —
አሁንም እስር ላይ ለሚገኙት የዞን ዘጠኝ አምደኞች አዲስ ቀጠሮ ተሰጠ
የፌድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት ክሳቸው ባልተቋረጠው የዞን ዘጠኝ አምደኞች ጉዳይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ሰጠ።
ክሳቸው ተቋርጦ በቅርቡ ከእስ የተለቀቁቁት ባልደረቦቻቸው በኤግዝቢትነት የተያዙባቸው ንብረቶቻቸው ይመለሱላቸው ዘንድ በጠየቁት መሠረት ድጋሚ ትዕዛዝ እንደሚሰጥም ችሎቱ አስታውቋል።