በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የረዥም ጊዜ የዚምባብዌ መሪ ሮበርት ሙጋቤ የቁም እሥር ላይ ናቸው

የረዥም ጊዜ የዚምባብዌ መሪ ሮበርት ሙጋቤ ከመኖርያ ቤታቸው እንዳይወጡ መደርጉን የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ተናግረዋል። ለሠላሳ ሠባት ዓመታት ያህል ሥልጣን ላይ የቆዩትን ሙጋቤ ከሥልጣን ለማስወገድ በወታደራዊ ኃይል የተደገፈ ሙከራ እየተካሄደ ይመስላል።

የረዥም ጊዜ የዚምባብዌ መሪ ሮበርት ሙጋቤ ከመኖርያ ቤታቸው እንዳይወጡ መደርጉን የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ተናግረዋል። ለሠላሳ ሠባት ዓመታት ያህል ሥልጣን ላይ የቆዩትን ሙጋቤ ከሥልጣን ለማስወገድ በወታደራዊ ኃይል የተደገፈ ሙከራ እየተካሄደ ይመስላል።

በመዲናይቱ ሃራሬ ውጥረት እንደሰፈነ የማኅበራዊ ሚድያ ወሬዎች አመልክተዋል፣ አንዳንድ የንግድ መደብሮች በጊዜ ተዘግተዋል።

ትላንት ሃራሬ ዙርያ ታንኮች ሲዘዋወሩ ታይተዋል። ፕሬዚዳንት ሙጋቤ የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ኢመርሰን ምናንጋግዋ ደጋፊዎችን ከገዢው /ZANU-PF/ ፓርቲ የማስወጣቱን ተግባር ካላቆሙ ቦታዉን እይዛለሁ ሲሉ የሀገሪቱ ወታደራዊ ኃይል ሃላፊ ጄኔራል ኮንስታንቲኖ ቺዌንጌ ባለፈው ሰኞ አስጠንቅቀው ነበር።

ፕሬዚዳንት ሙጋቤ ምክትል ፕሬዚዳንቱን ከሥልጣን ካባረሩ በኋላ በርካታ ሰዎች ታስረዋል።

ጄኔራል ቺዌንጌ መግለጫውን ከሰጡ በኋላ የሃገሪቱ ገዢ ፓርቲ ጄኔራሉን “በክህደት ተግባር” ከሷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG