ዋሺንግተን ዲሲ —
ዚምባብዌ ውስጥ ዋና ከተማዋ አቅራቢያ የሚገኝ ያረጀ የወርቅ ማእድን ማውጫ ጉድጓድ የተደረመሰባቸውን ቢያንስ ሰላሳ የሚሆኑ ሰራተኞች ለማውጣት የእርዳታ ሰራተኞች እየተሯሯጡ ናቸው።
ቤተሰቦቻቸው በጸሎት እና በስጋት እየተጠባበቁ ሲሆን የማዕድን ሰራተኞች ማህበር ተጠሪ እንዳሉ እስካሁን ስድስት ሰራተኞችን በህይወት ለማውጣት ተችሏል።
አደጋው የደረሰው ከሃሬሬ ወጣ ብላ የምትገኝ ቢንዲቱ የምትባል ከተማ ላይ መሆኑን ተገልጿል።
ዚምባብዌ ከውጭ ምንዛሬዋ ስድሳ ከመቶውን የምታገኘው ከወርቅ ማዕድኗ መሆኑ ተገልጿል።
የማዕድን አውጪዎች ወርቃቸውን ለመንግሥት በርካሽ ላለመሸጥ ሲሉ ህጋዊ ፈቃድ ሳያወጡ ቁፋሮ ላይ እንደሚሰማሩ ዜናው ጨምሮ አምልክቷል።