በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተቃዋሚ ዕጩ በሌለበት የሚወዳደረው የዚምባቡዌ ገዢ ፓርቲ “ብዙ መቀመጫ አሸንፋለሁ” እያለ ነው


የዚምባቡዌ ፕሬዚደንት ኤመርሰን ምናንጋጋዋ
የዚምባቡዌ ፕሬዚደንት ኤመርሰን ምናንጋጋዋ

ዚምባቡዌ ውስጥ ነገ ቅዳሜ ምክር ቤታዊ ምርጫ ይካሄዳል፡፡

የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ኤመርሰን ምናንጋጋዋ በማዕድን በከበረችው ሀገር ስልጣናቸውን እያጠናከሩ ባሉበት በዚህ ወቅት ምርጫው የሚካሄደው ዘጠኝ ክፍት የምክር ቤት መቀመጫዎችን ለመያዝ ሲሆን አብዛኞቹ የተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩዎች በምርጫው አይሳተፉም፡፡

የዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ “ለለውጥ የቆሙ ዜጎች ጥምረት” የምክር ቤት አባላት የምክር ቤት መቀመጫቸው መወሰዱን ተከትሎ የፖለቲካ ቀውሱ ተቀጣጥሏል፡፡

የሀገሪቱ ፍርድ ቤት ትናንት በሰጠው ውሳኔ አብዛኞቹ የተቃዋሚ ፓርቲው ዕጩዎች በነገው ምርጫ መወዳደር አይችሉም ብሏል፡፡

የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ካልቀለበሰው በስተቀር ሕገ መንግሥቱን ለመቀየር እየተንቀሳቀሰ ያለው ዛኑ ፕ ኤፍ በቀላሉ ተጨማሪ የምክር ቤት መቀመጫዎች ይወስዳል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG