ዋሺንግተን ዲሲ —
ዚምባብዌ ውስጥ በነዳጅ ዋጋ መናር የተቆጡ ዜጎች የአካሄዱት ተቃውሞ የዋና ከተማዋን እንቅስቃሴ ቀጥ አድርጎ መዋሉ ተገለፀ።
የሐራሬ ከተማን ያጥለቀለቀው ተቃውሞ ለበርካታ የንግድ ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶችና መሥሪያ ቤቶች መዘጋት ምክንያት መሆኑም ታውቋል። መነሾውም፣ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋዋ በነዳጅ ዋጋ ላይ ያሳለፉት ያልተጠበቀ ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ ጭማሬ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት የዚምባብዌ ንግድና የሠራተኛው ማሕበር የሦስት ቀን የሥራ ማቆም ዓድማ እንዲጠራ አስገድዷል።
ከሥራ ማቆም ዓድማው ጋር በተያያዘ፣ ከፖሊሶች ጋር ግጭት ተፈጥሮ ቢያንስ ወደ 2መቶ ሰዎች መታሰራቸውም ታውቋል
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ባለሥልጣን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዳይሰራ አድርገዋል በማለት የሐራሬ ነዋሪዎች ቅሬታ እያሰሙ መሆናቸው ተነገረ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ