በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዚምባቡዌ ፍ/ቤት በምርጫ ውጤቶች ላይ ከተቃዋሚዎች የቀረበውን ክስ ማድመጥ ጀመረ


የዚምባቡዌ ህገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ባለፈው ወር የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤቶች በሚመለከት ከተቃዋሚዎች የቀረበውን ክስ ዛሬ ረቡዕ ማድመጥ ጀምሯል።

የዚምባቡዌ ህገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ባለፈው ወር የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤቶች በሚመለከት ከተቃዋሚዎች የቀረበውን ክስ ዛሬ ረቡዕ ማድመጥ ጀምሯል።

የዚምባብዌ የምርጫ ኮሚሽን በቅርቡ የተካሄደውን ምርጫ ፕሬዚዳንቱን ኤመርሰን ምናንጋጋዋን እና ገዢ ፓርቲያቸውን ለመጥቀም ብሎ አጭበርብሯል ሲል የዲሞክራሲያዊ ለውጥ ንቅናቄ ፓርቲ ከሷል።

ይፋ በተደረጉት የምርጫው ውጤቶች መሰረት ምንንጋግዋ ሃምሳ አንድ ከመቶ ድምፅ አግኝተው አርባ አራት ከመቶውን ድምፅ ያገኙትን የተቃዋሚ /MDC/ ዕጩውን ኔልሰን ቻሚሳን አሸንፈዋቸዋል።

/MDC/ አስመራጭ ኮሚሽንኑን ለፕሬዚዳንት ምናናጋጋዋ የተሰጠውን ድምፅ ድምር አግዝፎ አቅርቧል። በአንዳንድ የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች የተቆጠረው ድምፅ ደግሞ ከተመዘገቡት መራጮች በላይ ነው ሲል ወንጅሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG