ዋሺንግተን ዲሲ —
በገንዘብ ዝውውር ላይ አዲስ የተጣለውን ህግ በመቃወም የሚወጣውን ሰልፈኛ እንደሚበትኑ፣ የዚምባብዌ ፖሊሶች አስታወቁ። አንድ የፖሊስ ቃል አቀባይ ዛሬ በሰጠው ቃል፣ ሀራሬ ላይ የተጠራ አንድ ሕዝባዊ ስብሰባ በኮሌራ ወረርሽኝ ምክንያት እንዲበተን የተደረገበትን ሁኔታ አስታውሷል።
ተቺዎች እንደሚናገሩት ከሆነ፣ የፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ደጋፊዎች ሰልፍ ማድረግ ከፈለጉ ይፈቀድላቸዋል፣ ተቃዋሚዎች ግን ሕዝባዊ ሰብሰባ እንኳ መጥራት አይፈቀድላቸውም።
ዚምባብዌ ውስጥ ኮሌራ የሃምሳ ሰዎችን ሕይወት ያጠፋ ሲሆን፣ ከ10,000 የማያንሱ ደግሞ በህመሙ ተይዘዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ