በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዚምባብዌ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ዛምቢያ ድንበር ላይ ተይዘው ታሰሩ


የዚምባብዌ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ቴንዳይ ቢቲ
የዚምባብዌ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ቴንዳይ ቢቲ

የዚምባብዌ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ቴንዳይ ቢቲ ዛምቢያ ድንበር ላይ ተይዘው ታሰሩ።

የዚምባብዌ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ቴንዳይ ቢቲ ዛምቢያ ድንበር ላይ ተይዘው ታሰሩ።

ጠበቃቸው ኢንኮቢዚታ ሚሊሎ እንደተናገሩት ቢቲ የተያዙት ወደዛምቢያ ድንበር አቁርጠው ገብተው ጥገኝነት ሊጠይቁ ሲሞክሩ ነው።

ቢቲ ባለፈው ሳምንት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ብጥብጥ ሊቀሰቅሱ ሞክረዋል ተብለው በዚምባብዌ ፖሊስ ከሚፈለጉ ዘጠኝ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ ንቅናቄ አባላት መካከል አንዱ ናቸው።

ድርጅቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ለፕሬዚዳንቱ ኤመርሰን ምናንጋዋ ተጭበርብሮላቸዋል ብሎ ወንጅሏል።

ቴንዳይ ቢቲ ፕሬዚዳነት ምናናጋግዋ ማሸነፋቸው በይፋ ከመታወጁ ከአንድ ቀን በፊት በተካሄደ ጋዜጣው ጉባዔ ላይ “በምርጫው የኤምዲሲው ዕጩ ኔልሰን ቻሚሳ አሸንፈዋል” ማለታቸው ይታወሳል።

የቻሚሳ ደጋፊዎች በማግሥቱ የምርጫውን ውጤት በመቃወም የተቃውሞ ሰክፍ ሲያደርጉ ፖሊስ በተኮሰው ጥይት ሥድስት ሰው ተገድሏል። ቴንዳይ ቢቲ ከ2009 እስከ 2013 በጊዜው ፕሬዚዳንት ከነበሩት ሮበርት ሙጋቤ ጋር ንቅናቄቸው መስርቶት በነበረው የሥልጣን ክፍፍል መንግሥት ውስጥ የገንዘብ ሚኒስትር ነበሩ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG