ዋሺንግተን ዲሲ —
ሮበርት ሙጋቤ ከረዥም ጊዜ ህመም በኋላ በ95 ዓመት ዕድሜያቸው ሲንጋፖር በሚገኝ ሆስፒታል ባለፈው አረብ ማረፋቸው የሚታወቅ ነው።
ሮይተርስ የዜና አገልግሎት በዘገበው መሰረት የሙጋቤ የቀበር ሥነ፡ስርዓት በመጪው ቅዳሜ በሀራሬ ብሄራዊ የስፖርት ስታድዮም እንደሚደረግ መንግሥት ለኤምባሲዎች መልዕክት ልኳል። የቀብር ሥነ ስርዓታቸውም በነገው ዕለት ይፈፀማል።