በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዚምባብዌ ምርጫ

የዚምባብዌ የሰብዓዊ መብት ታጋዮች በድኅረ ምርጫው በመዲናይቱ ሀረሬ የሦስት ሰዎች ህይወት ያጠፋውን የወታደሮች ዕርምጃን አውግዘዋል። የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዘገየ የተባለውን የምርጫ ውጤት በቅርቡ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

የዚምባብዌ የሰብዓዊ መብት ታጋዮች በድኅረ ምርጫው በመዲናይቱ ሀረሬ የሦስት ሰዎች ህይወት ያጠፋውን የወታደሮች ዕርምጃን አውግዘዋል። የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዘገየ የተባለውን የምርጫ ውጤት በቅርቡ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

በሕጉ መሰረት ውጤቱን ለማሳወቅ እስከ መጪው ቅዳሜ ድረስ ጊዜ እንዳላቸው ባሥስልጣኖቹ ተናግረዋል። በቅርቡ እንደሚያሳውቁም አውስተዋል።

ለፕሬዚዳንትነት የተወዳደሩት ተቃውሚ ኔልሰን ቻሚሳ ባለፈው ሰኞ አሸናፊ እኔ ነኝ ብለዋል። ትላንት ታድያ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የተቃዋሚው ፓርቲ ደጋፊዎች አምርጫ ኮሚሽኑ በር የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል። ሰልፈኞቹ በፖሊሶች ላይ ድንጋይ ወርውረዋል። ፖሊሶች ደግሞ ዕምባ አስመጪ ጋዝ ተኩሷል። የውሃ ግፊትም ተጠቅመዋል። ወደ ኋላ ደግሞ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በመንገዶች ሲዘዋወሩ ታይተዋል። ወታደሮች በመንገደኞች ላይ ሲተኩሱና ሰዎችን ሲደበድቡ እንደታዩ ተዘግቧል።

ፕሬዚዳንት ኢመርሰን ምናንግዋ ግጭቱ በነጻ አካል እንዲመረመር ዛሬ ጥሪ አቅርበዋል። ሀገሪቱ ወደ ፊት መንቀሳቀስ እንዳለባትም አስገንዝበዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG