በዚምባብዌ በቅርቡ ሊደረግ የታቀደው ምርጫ ሂደቱ ችግር ያለበት እና ዓለም አቀፋዊ መመዘኛ የሆነውን “ነጻ እና ፍትሃዊ” መመዘኛ እንደማያሟላ የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ ሂውማን ራይትስ ዎች አስታውቋል።
ዚምባብዌ በመጪው ነሐሴ 17 ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ብትሆንም፣ ውጥረት የተሞላበት እና ስርቆት ሊካሄድበት ይችላል ሲሉ ተንታኞች ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።
“የዚምባቡዌ ባለሥልጣናት አስተማማኝ፣ ነጻ እና ፍትሃዊ ምርጫ በማድረግ መሠረታዊ ነጻነትን ማክበር ተስኗቸዋል” ሲሉ የመብት ድርጅቱ የአፍሪካ አጥኚ እድሪስ አሊ ናሳህ ተናግረዋል።
“ባለሥልጣናት ጨቋኝ ህግጋትን በማውጣት ተቃዋሚዎችን አፍነዋል፣ ሁከትን እና ዛቻን በተቃዋሚዎች ላይ ፈጽማሉ” ሲል ድርጅቱ አስታውቋል።
“ፍርድ ቤቶች ተቃዋሚዎችን ኢላማ ለማድረግ የሚውሉ መሣሪያዎች ናቸው፣ የምርጫ ታዛቢዎችም ገለልተኛ አይደሉም” ሲል መሠረቱን አሜሪካ ያደረገው የመብት ተቆርቋሪ ድርጅት አስታውቋል።
መድረክ / ፎረም