በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዜምባቡዌ ፍ/ቤት የምርጫ ውጤቶች እንዲሰረዝ ተቃዋሚዎች ያስገቡትን አቤቱታ ውድቅ አደረገ


የዚምባቡዌ ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት በቅርቡ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤቶች እንዲሰርዝ ተቃዋሚዎች ያስገቡትን አቤቱታ ውድቅ አደረገው።

የዚምባቡዌ ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት በቅርቡ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤቶች እንዲሰርዝ ተቃዋሚዎች ያስገቡትን አቤቱታ ውድቅ አደረገው።

ፍርድ ቤቱ ዛሬ ዓርብ የሰጠው ብይን ሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ በሀገሪቱ ህገ መንግሥት መሰረት በአርባ ስምንት ሰዓት ውስጥ ቃለ መሃላቸውን እንዲፈጽሙ መንገዱን ከፍቶላቸዋል።

ይፋ በተደረገው የድምጽ ውጤት መሰረት ምናናጋግዋ ሃምሳ ነጥብ ስምንት ከመቶ ድምጽ አግኝተው በጠባብ የድምጽ ብልጫ አሸንፈዋል።

ተቃዋሚው ዕጩ ኔልሰን ቻሚሳ አርባ አራት ከመቶ ድምጽ ያገኙ ሲሆን የእርሳቸው የህግ ጠበቆች የምርጫው ውጤት ትክክል አይደለም ያሸነፉት ቻሚሳ ናቸው ብለው ተሟግተዋል።

በፍርድ ቤቱ የተገኙት ከዚህ ቀጥለው ምን እንደሚያደርጉ ወዲያውኑ አልተናገሩም፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG