ዋሺንግተን ዲሲ —
ዚምባብዌ ውስጥ ዛሬ ምርጫ ተካሂዷል። ለ38 ዓመታት ያህል በሮበርት ሙጋቤ ስትገዛ ከቆየች በኋላ የደቀቀው የሀገሪቱ ኢኮኖሚና ገፅታ ይሻሻላል የሚል እምነት እንዳለ ተገልጿል።
ሁለት ዋናዎቹ ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩ ሰዎች ዛሬ ማለዳ ድምፅ ሰጥተዋል። ሁለቱም እናሸንፋለን የሚል እምነት አላቸው። ዋናዎቹ ተወዳዳሪዎች ሙጋቤ ባለፈው ኅዳር ወር ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ ሥልጣኑን የተረከቡት ኤመርሰን ምናንግዋና የተቃውሞ መሪ ኔልሰን ቻሚሳ ናቸው።
በሀገሪቱ መዲና ሀራሪ ወጣት ድምፅ ሰጪዎች በብዛት መርጠዋል። ብዙዎቹ ከትላንት ሌሊት አንስተው ሰልፍ ይዘው እንደነበረ ተገልጿል። ሮልታ ታይካ የተባለች የ23 ዓመት እድሜ ወጣት። በጊዜ ድምፅ ለመስጣት ስለፈልኩኝ ስልፉ ይረዝምብኛል ብየ ስለፈራሁ እዚህ ነው ያደርኩት ብላለች።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ