በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዚምባብዌ የመንግሥቱ ኃይሎች በወሰዱት ዕርምጃ ሰዎች ተገደሉ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ዚምባብዌ ውስጥ - በነዳጅ ዘይት ዋጋ ላይ የተደረገውን ጭማሪ በመቃወም የወጡ ሰልፈኞች ላይ የመንግሥቱ ፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት ዕርምጃ በትንሹ 12 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች ከ 3መቶ በላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ዚምባብዌ ውስጥ - በነዳጅ ዘይት ዋጋ ላይ የተደረገውን ጭማሪ በመቃወም የወጡ ሰልፈኞች ላይ የመንግሥቱ ፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት ዕርምጃ በትንሹ 12 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች ከ 3መቶ በላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የውጭ ሀገሮች ጉብኝታቸውን አቋርጠው ትላንት ወደ ሃራሬ የተመለሱት ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ማናንጓ፡ ሁከቱን አስመልክቶ ምርመራ እንዲጀመርና ብሄራዊ ዕርቅ እንዲካሄድ ዛሬ ጥሪ አቅርበዋል።

የፖለቲካ ተንታኞች ግን ከ40 ዓመታት የሮበርት ሙጋቤ ጨቋኝ አስተዳደርና ሁከት በኋላ ምዕራፉን ለመዝጋት ቃል የገባው አዲሱ የኤመርሰን ማናንጓ መንግሥት ይህን የወቅቱን ሁኔታ ፈጥሯል ሲሉ ይከሳሉ።

ተቃውሞው ባለፈው ሣምንት የተጀመረው ፕሬዚዳንት ማናንጓ ዕርዳታ ለማሰባሰብ በታቀደ ወደ ውጭ ሀገሮች ከመሄዳቸው ጥቂት ቀደም ብለው በነዳጅ ዘይት ዋጋ ላይ የ150 በመቶ ጭማሪ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።

ተቃውሞው እያደገ መምጣቱ ያስደነገጣቸው የቀድሞው ወታደራዊ ኮማንደር ምክትል ፕሬዚዳንቱ ኮንስታንቲኖ ቺዌንጋ ስፋት ያለው አፋኝ ዘመቻ ጀምረዋል። በዚያም የፀጥታ ኃይሎች በሰልፈኞች ላይ መተኮስና ከመኖሪያ ቤታቸው እየጎተቱ አውጥተው መደብደብ ይዘዋል ተብሏል።

ፖሊሶች ባለፈው ሣምንት ዋና ከተማዋ ሃራሬ ውስጥ 5 ሰዎችን መግደላቸውና ሌሎች 25 ማቁሰላቸውንም የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች ጨምረው ያስረዳሉ።

የዚምባብዌ መንግሥት - በፀጥታ ኃይሎች የሚወሰደውን የኃይል ዕርምጃ እንዲያስቆም የተባበሩት መንግሥታት ጥሪ አስተላልፏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG