በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጃኮብ ዙማ በሙስና የተወነጀሉበትን ክስ አስተባበሉ


የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ

የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ በሙስና የተወነጀሉበትን ክስ አስተባበሉ፤ "ሙያዬንና ታዋቂነቴን ለማጣጣል፣ በመጨረሻምም እንድገደል የተውጠነጠነብኝ ሤራ ነው" ሲሉም ተሟግተዋል።

ዙማ ጆሃንስበርግ ውስጥ ለተሰየመው የምርመራ ኮሚሽን በሰጡት ቃል "ጠላቶቼ አገር ጥዬ እንድጠፋ የሸረቡብኝ ተንኮል" ነው ማለታቸውም ተሰምቷል።

"ኮሚሽኑ በማንም ላይ የተመሰረተ ክስን የማረጋገጥ ሥልጣን የለውም" ያሉት የምርመራ ኮሚሹኑ ዳኛ ሬይሞንድ በበኩላቸው፣ "የመመርመርና በቀረቡ ክሶች ዙሪያም ጥያቄ የማቅረብ ሥልጣን ነው ያለው" ብለዋል።

ዙማ፣ በበርካታ የሙስና ወንጀል በመጠርጠራቸው፣ ባለፈው ዓመት በገዥው የአፍሪካ ብሔራዊ ኰንግረስ/ANC/ ከሥልጣን እንዲወርዱ መደረጋቸው አይዘነጋም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG