በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዘለንስኪ ከባይደን እና ከአሜሪካ ሕግ አውጪዎች ጋራ ሊወያዩ ነው


የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ፣ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ፣ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ፣ ዛሬ ማክሰኞ ከዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት እና ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር ተገናኝተው፣ ሀገራቸው የሩሲያን ወረራ ለመዋጋት የሚያስችላትን እርዳታ ከዩናይትድ ስቴትስ ማግኘት በሚችሉበት መንገድ ላይ ይመክራሉ።

ዘለንስኪ ስብሰባዎቹን "በዚህ ዓመት በተገኙ ስኬቶች ላይ ተመስርተው በሚቀጥለው ዓመት ምን አይነት ውጤቶችን ማሳካት እንደሚችሉ" ለማስረዳት እንደሚጠቀሙበት ተናግረዋል።

የዩክሬን ወታደራዊ የአየር መከላከያን ለማስፋት ተጨማሪ ሚሳይሎች፣ ድሮኖች እና ጀቶች እንዲላክላቸው የሚሟገቱት ዘለንስኪ፣ ሰኞ እለት ዋሽንግተን በሚገኘው ብሄራዊ መከላከያ ዩንቨርስቲ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ዩክሬን 'ሰማዩን ማሸነፍ' አለባት ብለዋል።።

"ፖለቲከኖች ወታደሮቹን ለመክዳት ባይሞክሩ ይሻሻል። ምክንያቱም የጦር መሳሪያዎች ለመከላከል አስፈላጊ የሆኑትን ያክል፣ ነፃነትም ሁልጊዜ አንድነትን ይጠይቃል" ነው ያሉት ዘለንስኪ።

የዋይት ኃውስ የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፣ ባይደን በዩክሬን ስላለው የጦር ሜዳ ሁኔታ ከዘለንስኪ መረጃ እንደሚያገኙ ገልፀው፣ "ለዘለንስኪ እና ለዩክሬን ህዝብ፣ በተለይ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት እነሱን መደገፋችንን እንደምንቀጥል ግልፅ ያደጉላቸዋል" ብለዋል።

በተጨማሪም ባይደን፣ ለዩክሬን እና ለእስራኤል ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ለአሜሪካ ብሄራዊ ጥቅም ለምን አስፈላጊ እንደሆነ በግልፅ ያስረዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ከርቢ አመልክተዋል።

ባይደን ለዩክሬን እና ለእስራኤል የጦርነት ድጋፍ የሚውል 110 ቢሊዮን ዶላር የአሜሪካ ምክርቤት እንዲያፀድቅ የጠየቁ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ ከ61 ቢሊየን ዶላር በላይ የሚሆነው ለዩክሬን የሚሰጥ ይሆናል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG