በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዘለንስኪ ጀርመን ሀገራቸውን እንድትረዳ ተማጸኑ


የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚዪር ዘለንስኪ ለጀርመን ፓርላማ ንግግር ሲያደርጉ፤ በበርሊን፣ የሪችስታግ ሕንፃ እአአ መጋቢት 17/2022
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚዪር ዘለንስኪ ለጀርመን ፓርላማ ንግግር ሲያደርጉ፤ በበርሊን፣ የሪችስታግ ሕንፃ እአአ መጋቢት 17/2022

ፕሬዚደንቱ ዛሬ ሀሙስ ለጀርመን ፓርላማ ባደረጉት ንግግር

“አውሮፓ ውስጥ በነፃነት እና በባርነት መካከል ግንብ እየተገነባ ነው። ይህ ግንብ ደግሞ ዩክሬን ውስጥ ቦምብ በወደቀ እና አንዳች ውሳኔ ባልተወሰደ ቁጥር እያደገ የሚሄድ ነው" ብለዋል።

ዘለንስኪ በቪዲዮ አማካይነት ባደረጉት ንግግራቸው ጀርመን ከሩስያ ወደሀገሯ የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ ኖርድስትሪም 2 ግንባታ መደገፏን ከዩክሬን ደህንነት ይበልጥ ለራስዋ የኢኮኖሚ ጥቅም አድልታለች በማለት ነቅፈዋል። "ነግረናችሁ ነበር፤ ኖርድስትሪም የጦርነት ዝግጅት ነው ብለናችሁ ነበር" ብለዋል ዘለንስኪ።

ሩሲያ በከበበቻት ማሪዮፖል ከተማ የሚገኝ ትያትር ቤት የአየር ጥቃት ማድረሷን ዩክሬይን አስታውቃለች። ብዙ መቶ ሲቪሎች ከተጠለሉበት የትያትር ቤት ሰለባዎችን ለማውጥ እንቅስቃሴው ቀጥሏል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የዩክሬይኑ ፕሬዚዳንት ትናንት ያሰሙትን ተማጽኖ ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ የ800 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንድምታደርግ አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG