በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜሌንስኪ በፊሊፒንስ የሰላም ጉባኤውን በማስተዋወቅ ቻይናና ሩሲያን ተቹ


የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ከፊሊፒንስ ፕሬዝዳንት ፈርዲናንድ ማርኮስ ጁኒየር ጋር ሲገናኙ፣ ሰኞ ግንቦት 26 2016፣ (Jam Sta Rosa/Pool Photo via AP) © Provided by The Associated Press
የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ከፊሊፒንስ ፕሬዝዳንት ፈርዲናንድ ማርኮስ ጁኒየር ጋር ሲገናኙ፣ ሰኞ ግንቦት 26 2016፣ (Jam Sta Rosa/Pool Photo via AP) © Provided by The Associated Press

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ የፊሊፒንስ ፕሬዝዳንት ፈርዲናንድ ማርኮስ ጁኒየር በዩክሬን ጦርነት ላይ የሚካሄደውን ዓለም አቀፍ የሰላም ጉባኤ እንዲደግፉ አሳሰቡ።

ዜሌኒስኪ ይህን የተናገሩት ብዙም ባልተለመደው ድንገተኛው የእስያው ጉዟቸው ፊሊፒንስን በመግባት በዋና ከተማዋ ማኒላ ትላንት ዕሁድ ከፕሬዚዳንት ማርኮስ ጋር በተገናኙበት ወቅት ነው።

ማርኮስ ፊሊፒንስ በሰላም ጉባኤው ላይ እንደምትሳተፍ ቃል መግባታቸውን፣ የፊሊፒንስ ቃል አቀባይ ቼሎይ ጋራፊል ተናግረዋል።

ዜሌንስኪ “በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ቃል መግባትዎን ዛሬ ከእርስዎ በመስማቴ ደስተኛ ነኝ” በማለት “ይህ ትልቅ መልዕክት ነው” ሲሉ አክለዋል።

ዩክሬን ለወታደሮችዋ ተጨማሪ የአእምሮ ጤና ሠራተኞች እንደሚያስፈልጋት ዜሌንስኪ አፅንዖት ሰጥተዋል፡፡

ርዳታውን እንደሚሰጡ ቃል የገቡት ማርኮስ፣ ዩክሬን በዚህ ዓመት በማኒላ ኤምባሲዋን ለመክፈት መወሰንዋ ርዳታውን ያፋጥነዋል ብለዋል፡፡

ሁለቱም መሪዎች፣ ዋሽንግተንን ጨምሮ በርካታ የዓለም ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎችና ባለሥልጣናት በተገኙበት በሲንጋፖሩ ጉባኤ፣ ቻይናን በመተቸት፣ በአካባቢያዊ እና አለምአቀፋዊ ውጥረቶች ውስጥ ያላትን ሚና አጉልተው አሳይተዋል።

ዜለንስኪ ቻይና ሌሎች ሀገራት በጉባኤው እንዳይገኙ ጫና በማድረግ ሩሲያ የሰላም ጉባኤውን እንድታደናቅፍ ረድታለች ሲል ከሰዋል።

ቻይና በጦርነቱ ላይ ገለልተኝነቷን ገልጻለች፡፡ ይሁን እንጂ ግን ከሩሲያ ጋር ያላት የንግድ ልውውጥ የጨመረ ሲሆን የቻይና ስሪቶች በሩሲያ የጦር መሳሪያዎች ውስጥ እንደሚገኙ ተዘግቧል።

የዜሌነስኪን ክሶች አስመልክቶ ምላሽ እንዲሰጥ የተጠየቀውን የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተያየት ማግኘት አለመቻሉን አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG