በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜሌንስኪ ተጨማሪ የጦር መሣሪያ ዕርዳታ ጠየቁ


ፎቶ ፋይል፦ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ
ፎቶ ፋይል፦ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ

የሩሲያ ኃይሎች ዩክሬን ውስጥ የሚያደርሱትን ጥቃት መቀጠላቸውን የተናገሩ የዩክሬን ወታደራዊ ባለሥልጣናት ሀገራቸው ተጨማሪ የጦር መሣሪያ ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋት አሳስበዋል፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ታንኮች እና ሌሎችም የተራቀቁ የጦር መሳሪያዎች ለመላክ ቃል የሚገቡት ሀገሮች ቁጥር በመጨመሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

መሣሪያዎቹ ባፋጣኝ ይላኩልን ሲሉም ተማጽነዋል፡፡ “የሩሲያን ጥቃት መግታት የሚቻለው ተጨማሪ መሣሪያ ከተገኘ ብቻ ነው፡፡ ሽብርተኛው መንግሥት ከዚያ ሌላ የሚገባው ነገር የለም” ብለዋል ዜሌንስኪ፡፡

ሩሲያ ትናንት በብዙ የዩክሬን አካባቢዎች አዲስ የሚሳይል ጥቃት የከፈተች ሲሆን አስራ አንድ ሰው ሲገደል ሌሎች አስራ አንድ ሰዎች መቁሰላቸውን የዩክሬን ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ድርጅት ዋና ይሬክተር ራኣኤል ማሪያኖ ግሮሲ በሰጡት ቃል በዩክሬኑ የዛፖሮዢዢያ የኒውክሊየር ጣቢያ አጠገብ በየቀኑ ፍንዳታ እየተሰማ መሆኑን የድርጅቱ የደህንነት ባልደረቦች መናገራቸውን አመልክተዋል፡፡ ትናንት ሀሙስ እና ረቡዕም ፍንዳታ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡

ሩሲያ እና ዩክሬን የኒውክሌር ጣቢያው የጥቃት ዒላማ እንዳይደረግ በጣቢያው ዙሪያ የጸጥታ ቀጣና ለመከለል እንዲስማሙ የአይኤኢኤ ኃላፊው ራፋየል ማሪያኖ ግሮሲ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG