በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዛምቢያ ምርጫ ተቃዋሚው መሪ አሸነፉ


ሃካይንዴ ሂቺሌማ
ሃካይንዴ ሂቺሌማ

በዛምቢያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተቃዋሚ መሪው ሃካይንዴ ሂቺሌማ አሸነፉ።

የዛምቢያ የምርጫ ኮምሽን ዛሬ ሰኞ በዋና ከተማዋ ሉሳካ በሰጠው መግለጫ ሂቼሌማ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ በተካሄደው ምርጫ ከተሰጠው ድምፅ ከሃምሳ ከመቶ የሚበልጠውን ከ2 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ አግኝተዋል። ሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዚዳንት ኤድጋር ሉንጉ 1ነጥብ 8 ሚሊዮን ድምፅ አግኝተዋል።

የሃምሳ ዘጠኝ ዓመቱ ባለብዙ ሃብት ነጋዴው የአንድነት ለብሄራዊ ልማት ፓርቲው መሪ ሂቼሌማ ካሁን ቀደም አምስት ጊዜ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የተወዳደሩ ሲሆን መሪነቱን ለአሸናፊነት የበቁት ስድስተኛቸው ነው።

በምርጫው የተሸነፉት ፕሬዚዳንት ሉንጉ ቅዳሜ ዕለት የምርጫ ኮምሽኑ የመጀመሪያ የድምጽ ውጤቶችን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ "ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ አልነበረም" ሲሉ አውግዘዋል። በደጋፊዎቻቸው እና እና በገዢው ፓርቲያቸው አባላት ላይ "ጥቃት ሲፈጸምባቸው ነበር" ሲሉም ወንጅለዋል።

XS
SM
MD
LG