በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

19 ኢትዮጵያውያን በህገ-ወጥ አጓጓዦች መኪና ውስጥ እንዳሉ በአየር እጦት መሞታቸው ተገለጸ


ሉሳካ ከተማ
ሉሳካ ከተማ

ከትናንት በስቲያ ረቡዕ የሞቱት 19 ፍልሰተኞች ሱማላዊያን ናቸው ተብሎ ቀደም ሲል ተዘግቦ ነበር። ዛንብያ ውስጥ የናዶላ ከተማ ኗሪ የሆኑና መሓመድ አብዱላህ የተባሉ ሱማላዊነጋዴ፣ ሞተው የተገኙት ፍልስተኞች ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ለቪኦኤ ሶማልኛ አገልግሎት አረጋግጠዋል።

አንድ የዛምቢያ ባለሥልጣንም ፍልሰተኞቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን በማረጋገጥ የሚከተለውን መግለጫ ሰጥተዋል።

መለያ ቁጥሩ AFB 496 የሆነውና ንብረትነቱ የNdola BM ትራንስፖርት መሥሪያ ቤት የሆነው የዛምብያ የጭነት መኪና በኮንጎ ባለሥልጣናት ተጠልፎ እንደነበር ላረጋግጥ እወዳለሁ። ከጭነት መኪና ውስጥ የጓጓታ ድምፅ የሰሙ አሽከርካሪዎች፣ ሁኔታውን ለባለሥልጣናት በመግለጻቸው፣ የኮንጎ ባለሥልጣናትም የጭነት መኪናውን ሲፈትሹ፣ በርካታ አሳና ጥራ-ጥሬ (በቆሎ) ከተሞሉ ጆንያዎች ጋር 73 ኢትዮጵያውያን አገኙ። የጭነት መኪናው ሲከፈት 11 ሞተዋል። ቆይቶም የሟቾቹ ቁጥር ወደ 19 ከፍ ማለቱን ተገልጿል። ያሟሟታቸው ሁኔታ እየተጣራ ቢሆንም፣ ከመጨናነቅና ከመታፈን የተነሳ አየር በማጣታቸው እንደሆነ ተገምቷል። አስከሬናቸውም ወደ ዛምቢያው የናዶላ ማዕከላዊ ሆስፒታል ተልኳል።

የ29 ዓመቱ የጭነት መኪናው ነጂና፣ የ37 ዓመቱ ረዳቱ ሾፌር፣ ከሌሎች 54 ኢትዮጵያውያን ተጓጓዦች ጋር፣ ወደ ናዶላ ተወስደዋል። የዛምቢያው ናዶላ መሥሪያ ቤት፣ ከዓለማቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር፣ በሕይወት የተረፉት እንደ መጠለያ፣ መግብ፣ የመጠጥ ውኃ፣ መድኃኒትና አልባሳት ሊያገኙ ይችሉ ዘንድ ወደ ሉሳካ ለማጓጓዝ እየጣረ መሆኑ ታውቋል። ብዙዎቹ፣ ከድካም የተነሳ ዝለውና መንቀሳቀስ ተስኗቸው ተስተውለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ዓለምአቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት-IOM-እንደገለጸው፣ በዚህ ዓመት ብቻ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሞከሩ ቢያንስ 120,000 ፍልሰተኞች በኒጀር በኩል አልፈዋል። በህገ-ወጥ አሸጋጋሪዎች ግዴለሽነት የተነሳ የሞቱትና ድርጅቱ እስካሁን በይፋ የመዘገባቸው ፍልሰተኞች ቁጥር ግን፣ 34 ነው። ይህም፣ ባጠቃላይ ወደ አውሮፓ ለመፍለስ ሲሞክሩ ሰሓራ ምድር ላይ የሞቱትን ፍልሰተኞች አጠቃላይ ቁጥር 471 ያደርሰዋል። የሞቱት ፍልሰተኞች ጠቅላላ ድምር፣ ምናልባት ከፍ ሊል እንደሚችልም፣ ዓለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት አመልክቷል። እንደ ድርጅቱ አገላለጽ፣ አያሌ ሴቶች፣ በተፈራራቂ ወንዶች ከመጠን ባለፈ የወሲብ ግንኙነት ሕይወታቸው አልፏል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

19 ኢትዮጵያውያን በህገ-ወጥ አጓጓዦች መኪና ውስጥ እንዳሉ በአየር እጦት መሞታቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:58 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ



XS
SM
MD
LG