በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩቲዩብ የሩሲያ መንግሥት የዜና ተቋማት ላይ ገደብ ጣለ


ዩቲዩብ
ዩቲዩብ

ዩቲዩብ የተሰኘው ማኅበራዊ መገናኛ አውታር የሩሲያ መንግሥት ልሳን የሆነው ሩሲያ ቱደይ የዜና ተቋም እና ሌሎች ቻናሎች ከዩቲብ ገጻቸው የሚገኙትን ገቢ አግዷል። ይሄ እርምጃ ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ ፌስቡክ የተባለው አውታር ከወሰዳቸው እርምጃዎች ጋር የሚመሳሰል ነው።

ከዚህ በተጨማሪ አወታሮቹ ከዩቲዩብ ጥቆማ ላይ አልፎ አልፎ ብቻ ብቅ እንዲሉ እንደሚደረግ፣ በዩክሬን መንግሥት ጥያቄ መሰረት በሀገሪቱ ውስጥ እንዳይታዩ እንደሚታገዱም ተቋሙ አስታውቋል።

የዩክሬን ዲጂታል ሚኒስትር ማይካይሎ ፌድሮቭ ቅዳሜ ዕለት በቲዊተር ገጻቸው ላይ የሩሲያ ፕሮፖጋንዳ ጣቢያዎች ያሏቸው፣ ሩሲያ 24፣ ታስስ፣ ሪያ ኖቫስቲ የዜና አወታሮች እንዲታገዱ ዩቲዩብን መጠየቃቸውን አስታውቃል።

ሩሲያ ቱደይ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል። ሩሲያ ከአውሮፓዊያኑ 2018 ታህሳስ ወር በፊት ባሉት ሁለት ዓመታት ብቻ ከ26 የዩቲዩብ ጣቢያዎች ከ7 እስከ 32 ሚሊየን ዶላር እንዳገኘች ኦሜላስ የተባለ የዲጂታል አጥኝ ድርጅት ለሮይተርስ ተናግሯል።

XS
SM
MD
LG