በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ለሥራ አጥ ቁጥር መጨመር አባባሽ ምክኒያት መሆኑ ተነገረ


የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ለሥራ አጥ ቁጥር መጨመር አባባሽ ምክኒያት መሆኑ ተነገረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:30 0:00

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ለሥራ አጥ ቁጥር መጨመር አባባሽ ምክኒያት መሆኑ ተነገረ

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ለሥራ አጥ ቁጥር መጨመር አባባሽ ምክንያት ሆኗል ሲሉ የፌዴራል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ተናግረዋል።

የፌዴራል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ከአሜሪካ ድምፅ ጋር በነበራቸው ቆይታ በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል በተፈጠረው ጦርነት ሳቢያ ጥናት በተደረገባቸው የአማራ እና አፋር ክልሎች የሥራ አጥ ቁጥር እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል ብለዋል።

በሃገሪቱ ያለውን የሥራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ መሥሪያ ቤታቸው ገበያውን መሰረት ያደረገ ሥልጠና ለመስጠት መዘጋጀቱንም ሚኒስትሯ ገልፀዋል።

ከዚህ በፊት በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች ተመርቀው ሥራ ፈላጊ ለሆኑ ወጣቶች እንደገና ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት ላይ መሆኑንም አክለው ተናግረዋል።

ሚኒሰቴር መሥሪያ ቤታቸው በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት የወደሙ ኢንተርፕራይዞችን መልሶ ለመገንባት የሚውል የ180 ሚሊዮን ብር የሚገምት የቁሳቁስና የገንዝብ ድጋፍ አድርጓል።

በሌላ በኩል በሰሜን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተጀመረበት ትግራይ ክልል በተመሳሳይ ቀደም ሲል የመንግሥት ሠራተኞች የነበሩ ወጣቶች ጭምር ሥራ እንደሌላቸው በዚያ የሚገኘው ዘጋቢያችን በተለያየ ጊዜ ያጠናቀራቸው ዘገባዎች ያስረዳሉ። ሆኖም በፌዴራል መንግሥቱ አማካኝነት እንዲህ ያሉ ከጦርነቱ ጋር ተያይዘው ጥናቶች ሲደረጉና ሪፖርቶች ሲወጡ ትግራይ ክልልን ያካተቱ አይደሉም።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG