በአማራ ክልል አጣዬ ከተማ ውስጥ በተደጋጋሚ በተነሳው ግጭት ምክኒያት ከቤተሰቦቿ ጋራ ሦስት ጊዜ ተፈናቅላ የነበረችው ወጣት ገሊላ አሰፋ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያና ወደ ከፍተኛ ትምርት ቤት መግቢያ የላቀ ውጤት ካስመዘገቡት ሴት ተማሪዎች አንዷ ነች። በተለይ ላለፉት ሁለት ዓመታት የተረጋጋ ሕይወት እንዳልነበራት የገለፀችው ገሊላ አሰፋ በ2013 ዓ.ም አጣዬ ውስጥ የወላጆቿና የዘመዶቿ ቤቶች በሙሉ መውደማቸውን ትናገራለች።
በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሰች ተምራም ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባለች። “አስበነውም ይሁን ሳናስበው የጠበቅነውም ሆነ ያልጠበቅነው ችግሮች ያጋጥሙናል” የምትለው ገሊላ ሁሉም ነገር ያልፋል ብላ በማሰብ በፅናት መጓዟን ትናግራናለች፡፡ ገሊላን ለዛሬው የሴቶች ቀን እንግዳ አድርገናታል።
ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።