የትነበርሽ ንጉሤ ለአካል ጉዳተኞች መብት መሟገት የጀመረችው በዩኒቨርስቲ የሕግ ትምህርቷን በመከታተል ላይ በነበረችበት ወቅት ነው፡፡ በዩኒቨርስቲ አስተዳደር ውስጥ እርሷን ጨምሮ፣ ለአይነ ስውራን ተማሪዎች የብሬይል መጽሕፍ እንዲዘጋጅ አስተዋፅዖ አድርጋለች፡፡
የትነበርሽ ንጉሤ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የአካል ጉዳተኞችና መብት፣ የግንዛቤ ማስጨበጫና ሰብዓዊ መብቶችና ዕድሎች ለመሟገት የሕግ ሞያ ስራዋን በመተው የሙሉ ጊዜዋን ሰጥታ እየሰራች ትገኛለች፡፡
በሠራችው እና በአበረከተችው አስተዋፆዖ በዘንድሮም በየዓመቱ በስዊድን ስቶክሆልም በሚካሄደው "የራይት ላይቭሊ ሁድ አዋርድ" ፋውንዴሽን ሽልማት አግኝታለች፡፡
የትነበርሽ ንጉሤ ለአሶሼትድ ፕሬስ እንደገለፀችው በማይመች ሁኔታ፣ መሰረትዊ መብቶቻቸው የተነፈጋቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ አካል ጉዳተኞች መኖራቸውን ችሎታ፣ አቅምና ብቃት እያላቸው ዕድሎችን መነፈጋቸውን ትናገራለች፡፡
ከአሜሪካ፣ ጀርመንና በስዊዘርላንድ ከሚገኙ መሰል ተቋማት ጋር በትብብር የሚሰራው ራይት ላይቭሊ ሁድ አዋርድ ፋውንዴሽን ለተለያዩ የዓለማችን ችግሮች ተግባራዊ መፍትሄዎችን ለማምጣት ለሠሩ ታታሪ ግለሰቦችና ድርጅቶች ዕውቅና የሚሰጥ፣ ለሰዎች ህይወት መሻሻል አውንታዊ አስተዋፅዖ ያበረከቱ ግለሰቦችን በማበረታታት ትኩረቱ አድርጎ የሚሰራ ዓለምቀፍ ድርጅት ነው፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ