በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የየመን የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲቆም ተጠየቀ

Yemen's War
Yemen's War

የመን ውስጥ የሚዋጉት ሁሉም ወገኖች ብጥብጡን አቁመው የእርስ በእርስ ጦርነቱን የሚያከትም ፓለቲካዊ ንግግር እንዲጀምሩ ዩናይትድ ስቴትስም ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር ጠይቃለች ።

የመን ውስጥ የሚዋጉት ሁሉም ወገኖች ብጥብጡን አቁመው የእርስ በእርስ ጦርነቱን የሚያከትም ፓለቲካዊ ንግግር እንዲጀምሩ ዩናይትድ ስቴትስም ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር ጠይቃለች ።

አማፅያኑ አጋራቸው የነበሩትን የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳልህን መግደላቸውን ተከትሎ ውጥረቱ ይባባሳል የሚል ሥጋት ፈጥሯል።

ትናንት የዩናይትድ ቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሄዘር ኖወርት ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ስለየመኑ ሁከት ከፍተኛ ሥጋት ላይ ነን ብለዋል።

ሁሉም ወገኖች ውጊያውን እንዲያቆሙና የቀድሞው ፕሬዚዳት መገደል ውጊያውን ማባባስ ምክንያት ከማድረግ እንዲቆጠቡ ዩናይትድ በማሳሰብ ላይ መሆኗን አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣን ለቪኦኤ ገልፀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG