በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የየመን ሁቲዎች ለእስራኤል የጋዛን የእርዳታ እገዳ እንድታነሳ የአራት ቀናት ቀነ ገደብ ሰጡ 


ፎቶ ፋይል፡ በግሪክ ባንዲራ በምትንቀሳቀስ የነዳጅ ጫኝ መርከብ በሁቲ አማጽያን ጥቃት ከደርሰባት በኋላ ጭስ ሲወጣ ያሳያል፣ ነሐሴ 17ቀን 2016 ዓ.ም.
ፎቶ ፋይል፡ በግሪክ ባንዲራ በምትንቀሳቀስ የነዳጅ ጫኝ መርከብ በሁቲ አማጽያን ጥቃት ከደርሰባት በኋላ ጭስ ሲወጣ ያሳያል፣ ነሐሴ 17ቀን 2016 ዓ.ም.

የየመን ሁቲ አማጽያን መሪ እስራኤል በአራት ቀናት ውስጥ በጋዛ ላይ የጣለችውን የእርዳታ እገዳ ካላነሳች ቡድኑ በእስራኤል ላይ የሚያደርገውን የባህር ሃይል ጥቃት እንደሚቀጥል ትላንት አስታውቋል፡፡

ይህም እ.ኤ.አ. በጥር ወር የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ እየቀነሰ የመጣው የሁቲዎች ጥቃት ሊባባስ እንደሚችል የሚጠቁም ነው ተብሏል፡፡

ኢራን አጋር የሆኑት የሁቲ አማጽያን እስራኤል በጋዛ በዩናይትድ ስቴትስ በሽብር የተፈረጀው ሃማስ ቡድን ላይ በከፈተችው ጦርነት ምክንያት ለፍልስጤማውያን አጋርነት ለማሳየት በሚል ከእአአ ህዳር 2023 ጀምሮ በመርከብ ላይ ያነጣጠሩ ከ100 በላይ ጥቃቶችን ፈጽሟል፡፡

መሪው አል-ሁቲ በኩል "ለአራት ቀናት ቀነ ገደብ እንሰጣለን፡ ይህም የጊዜ ገደብም ለጋዛ የተኩስ አቁም አሸማጋዮች ለጥረታቸው ሲባል ነው" ብሏል፡፡

እ.ኤ.አ መጋቢት 2 ጀምሮ እስራኤል የእርዳታ መኪኖችን ወደ ጋዛ እንዳይገቡ አግዳለች፡፡ ሃማስ እርዳታዎችን በመስረቅ ለፍልስጤማውያን እንዳይደርስ አድርጓል ስትልም ትከሳለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG