ከዘጠኝ ወር በፊት የተደረሰው የየመን ጦርነት ተፋላሚዎች የተኩስ አቁም ውል አሁንም እንደጸና መሆኑ ተዘግቧል። የእርስ በርስ ውጊያው ለዚህ ያህል ጊዜ ሳይፈርስ ሲቆይ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተመልክቷል።
የየመን የሳውዲ አረቢያ እና የተመድ ባለሥልጣናት እንዳሉት ሳውዲ አረቢያ እና ተቀናቃኞቿ በኢራን የሚደገፉት ሁቲዎቹ አማጽያን ተኩስ አቁሙ ሊጠናከር እና ወደ ለረጅም ጊዜ የቆየውን ጦርነት ወደሚያቆም ሥምምነት መሸጋገር ስለሚችልበት መንገድ እየተነጋገሩ መሆናቸው ተዘግቧል።
ድርድሩ መቀጠሉ ውጊያው እንዳያገረሽ ቢያደርግም ሁለቱ ወገኖች አሁንም የማያስማሟቸው ዋና ዋና ጉዳዮች እንዳሉ ተመልክቷል።
ሁቲዎቹ አማጽያን የተዘጉት የአየር እና የባህር መስመሮች እንዲከፈቱላቸው ይፈልጋሉ። በተቀናቃኞቻቸው ቁጥጥር ስር ካለው የነዳጅ የነዳጅ ሀብት ከሚገኘው ገቢ ለመንግሥት ሰራተኛ እና የጦር ኃይል ደመውዝ ክፍያ የሚሆን ገንዘብ ይስጠን ሲሉ ጠይቀዋል።
ሳውዲ በበኩሏ ሁቲዎቹ አማጽያን የደህንነት ዋስትና እንዲሰጡ ጠይቃለች። ጦርነቱን ለማቆም ከሌሎቹ ተፋላሚ ቡድኖች ጋር ድርድር እንዲያካሂዱም ትፈልጋለች።