በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍልሰተኞችን የያዘ ጀልባ በየመን ባሕር ዳርቻ ሰመጠ


ከአፍሪካ ቀንድ የተነሡ ፍልሰተኞችን የያዘ ጀልባ፣ በየመን የባሕር ዳርቻ እንደሰመጡና የጠፉትን 49 ተሳፋሪዎች ፍለጋ ላይ እንደኾኑ፣ የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ትላንት እሑድ 75 ፍልሰተኞችን ይዞ ሲጓዝ ከነበረው ጀልባ 26ቱ እንደተረፉ፣ የየመን የባሕር ደንበር ጥበቃ ባለሥልጣናት ገልጸዋል።

የጠፉት ተሳፋሪዎች ፍለጋ፣ ዛሬ ሰኞም እንደቀጠለ ታውቋል።

ጀልባዋ የሰመጠችው፣ በከፍተኛ ነፋስ ምክንያት እንደኾነና ተሳፋሪዎቹ በሙሉ ወደ ውኃው እንደወደቁ፣ ሳባ የተሰኘው የመንግሥት ዜና አገልግሎት፣ የባሕር ደንበር ጥበቃ ባለሥልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል።

ለተሻለ ኑሮ ወደ ባሕረ ሰላጤው ሀገራት የሚጓዙና ከኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እና ሶማሊያ የሚነሡ ፍልሰተኞች፣ ተመሳሳይ ተደጋጋሚ አደጋ ሲገጥማቸው ይስተዋላል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG