በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትስ ስም የተመዘገበ መርከብ በየመን ሁቲ ታጣቂዎች ተተኮሰበት


አረቢያ ባሕር
አረቢያ ባሕር

የየመን ሂቲ ታጣቂዎች በዩናይትድ ስቴትስ ሥር የተመዘገበ ዕቃ አጓጓዥ መርከብ ትላንት ማክሰኞ በአረቢያ ባሕር በማለፍ ላይ ሳለ እንደተኮሱበት ተነገረ፡፡

የዩናይትድ ኪንግደም የማሪታይም ንግድ እንቅስቃሴ ተቋም በሰጠው መግለጫ ሜርስክ ሴንቶሳ የተባለው መርከብ በየመን “ኒሽቱን” ጠረፍ አቅራቢያ ሲደርስ ፍንዳታ መድረሱን የመርከቡ ካፒቴን አስታውቀዋል፡፡

የታጣቂው ቡድን ቃል አቀባይ ትላንት ማታ ባወጣው መግለጫ መርከቡ ላይ ለደረሰው ጥቃት እንዲሁም በየመን ባሕረ ሰላጤ ላይ በሚያልፉ ሁለት ሌሎች መርከቦች ላይ ለደረሱት ጥቃቶች ኅላፊነት ወስዷል፡፡ የመርስክ ሴንቶሳ መርከበኞች በሙሉ ጉዳት እንዳልደረሰባቸው የእንግሊዙ የንግድ መርከብ እንቅስቃሴዎች ድርጅት አመልክቷል፡፡

ታጣቂ ሁቲዎች ካለፈው ሕዳር ወር ጀምረው በቀይ ባሕር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ በኩል በሚያልፉ የንግድ መርከቦች ላይ በሰው አልባ አውሮፕላን እና በሚሳይል ጥቃት ሲያካሂዱ ቆይተዋል፡፡ ጥቃቱን የሚያደርሱት ጋዛ ላይ በሚካሄደው ጦርነት ፍልስጥኤማዊያንን በመደገፍ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ በአጸፋው የዩናይትድ ስቴትስ እና የእንግሊዝ ኅይሎች የመን ውስጥ ያሉ የሁቲ አማጽያን ይዞታዎችን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶችን ሲያካሂዱ ቆይተዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG