በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመናውያን ፍልስጤማውያንን በመደገፍ በሰነዓ ሰልፍ አደረጉ


የሁቲ አማጺያን ደጋፊዎችን ጨምሮ በሺህ የሚቆጠሩ የመናውያን በጋዛ ከሚገኙ ፍልስጤማውያን ጋራ ያላቸውን አንድነት ለመግለጽ ዛሬ በሰነዓ ሰልፍ አካሂደዋል።
የሁቲ አማጺያን ደጋፊዎችን ጨምሮ በሺህ የሚቆጠሩ የመናውያን በጋዛ ከሚገኙ ፍልስጤማውያን ጋራ ያላቸውን አንድነት ለመግለጽ ዛሬ በሰነዓ ሰልፍ አካሂደዋል።

የሁቲ አማጺያን ደጋፊዎችን ጨምሮ በሺህ የሚቆጠሩ የመናውያን በጋዛ ከሚገኙ ፍልስጤማውያን ጋራ ያላቸውን አንድነት ለመግለጽ ዛሬ በሰነዓ ከፍተኛ ሰልፍ አካሂደዋል።

የየመን መዲናን እና ሕዝብ በብዛት የሚኖሩባችውን አብዛኛውን የየመን መሬት የተቆጣጠሩት የሁቲ አማፂያን፣ የእስራኤል እና ሐማስ ጦርነትን ተከትሎ በቀይ ባሕር ላይ የሚመላለሱ መርከቦችን ሲያጠቁ ሰንብተዋል።

ጥቃቶቹ እስራኤልን በመቃወም እና ለፍልስጤማውያን ያላቸውን ድጋፍ ለመግለጽ መሆኑን አማፂያኑ ይገልጻሉ።ከትናንት በስቲያ ረቡዕ አማፂያኑ “ትሩ ከንፊደንስ” በተሰነች ደረቅ ጭነት አመላላሽ መርከብ ላይ በሚሳዬል ባደረሱት ጥቃት ሦስት የመርከቡ ሠራተኞች መገደላቸውን የመርከቧ ባለቤቶች እና ሥራ አስኪያጆች አስታውቀዋል።

አማፂያኑ በሚያደርሱት ጥቃት ከዓለም 12 በመቶ የሚሆነው የንግድ ሸቀጥ የሚመላለስባት ቀይ ባሕር እና የሱወዝ ካናል ያለው የመርከቦች ዝውውር ተስተጓጉሏል። መርከቦቹ በአፍሪካ ደቡባዊ ክፍል እንዲዞሩና ረጅም ጉዙ እንዲያደርጉ በመገደዳቸው፣ የሸቀጦች ዋጋ እንዳያሻቅብ ተሰግቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG