በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በየመን የኮሌራ ወረርሽኝ በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑ ተገለፀ

የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የጤና ድርጅት በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀው የመን ውስጥ እስካሁን በኮሌራ ወረርሺኝ ከተጠቁት ሃምሳ ሺሕ ሰዎች በተጨማሪ በቀጣዮቹ ስድሥት ወራት ውስጥ ሁለት መቶ ሽሕ ሰው በበሽታው ይያዛል።

የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የጤና ድርጅት በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀው የመን ውስጥ እስካሁን በኮሌራ ወረርሺኝ ከተጠቁት ሃምሳ ሺሕ ሰዎች በተጨማሪ በቀጣዮቹ ስድሥት ወራት ውስጥ ሁለት መቶ ሽሕ ሰው በበሽታው ይያዛል።

የዓለም የጤና ድርጅት የየመን ተወካይ ኔቪዮ ዛጋሪያ የአሁኑ የኮሌራ ወረርሽኙ እያተዛመተ ያለበት ፍጥነት ከአሁን ቀደም ታይቶ የማያውቅ ነው ብለዋል።

እስካሁን የሞቱት ሰዎች ቁጥር ሁለት መቶ አርባ ደርሷል። ባለፉት ሦስት ሳምንታት ውስጥ ከሃምሳ ሺሕ በላይ በበሽታው ተይዘዋል።

በሁቲ አማፅያን እና በሳውዲ በሚመሩ የአረብ ሀገሮች ወታደራዊ ሕብረት የሚታገዙት የመንግሥት ሃይሎች ውጊያ ሁለት ዓመት ያስቆጠረ ሲሆን ከሥምንት ሺሕ በላይ ህዝብ አልቆበታል።

የመን በኮሌራ ወረርሺኝ ምክንያት ትናንት በዋና ከተማዋ ሰንዓ አስቸኳይ ጊዜ አውጇል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG