በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰማንያኛው የሰማዕታት ቀን


የካቲት 12 የሰማዕታት አደባባይና መታሰቢያ ኃውልት
የካቲት 12 የሰማዕታት አደባባይና መታሰቢያ ኃውልት

የዛሬ ሰማንያ ዓመት በፋሺስት ጣልያን ወራሪ ጦር ከሰላሣ ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን አዲስ አበባ ላይ የተጨፈጨፉበት የሰማዕታት ቀን ዛሬ በኢትዮጵያና በዓለም ዙሪያ ባሉ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ታስቦ ውሏል፡፡ ቫቲካን ለፋሺስቶች አበርክታ ለነበረው ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ድጋፍ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ፤ የኢጣልያ መንግሥት ለኢትዮጵያ ተገቢውን ካሣ እንዲከፍል ይሚሉና ሌሎች ጥያቄዎችን የሚያነሳ ቡድን ስለጥያቄዎቹ በስፋት ያስረዳል።

በሌላ በኩል ደግሞ የፋሺስት ጣልያን መሪ ቤኒቶ ሙሶሊኒ የምሥራቅ አፍሪካ እንደራሴና የሸዋ ጠቅላይ ገዥ አድርጎ ሾሞት ለነበረው ሩዶልፎ ግራዚያኒ አፊሊ የምትባል ከተማ ውስጥ ቆሞ የነበረውን ሐውልት የሃገሪቱ መንግሥት መውረሱንና ሐውልቱን ያሠራው ግለሰብም በቁጥጥር ሥር ውሎ እንደተፈረደበት ከትናንት በስተያ ዋሺንግተን ዲሲ የሚገኘው ጣልያን ኤምባሲ ገብተው ከነበሩ ኢትዮጵያዊያን አንዱ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል፡፡

ዓለምአቀፍ ኅብረት ለፍትሕ - የኢትዮጵያ ጉዳይ የሚባለውን በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የሚያንቀሳቅሱትን ቡድን መልዕክት ይዘው ወደ ኤምባሲው የገቡት አቶ ፍፁም አቻምየለህ የኤምባሲውን ተጠሪ ማነጋገራቸውን አመልክተዋል፡፡

የኅብረቱ የሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር አቶ ኪዳኔ ዓለማየሁ በአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ በተዘጋጀ ውይይት ላይ በሰጡት ማብራሪያ የኅብረቱ መሠረታዊ ዓላማዎች ቫቲካን ለፋሺስቶች አበርክታ ለነበረው ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ድጋፍ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ፤ የኢጣልያ መንግሥት ለኢትዮጵያ ተገቢውን ካሣ እንዲከፍል፤ ቫቲካንና ኢጣልያ የተዘረፉ ንብረቶችን ለኢትዮጵያ እንዲመልሱ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፋሺስቶች በኢትዮጵያ ላይ የፈፀሙትን የሰውን ዘር የማጥፋት ወንጀል በመዝገቡ እንዲያውል፤ ለግፈኛው ወንጀለኛ ለግራዚያኒ የተቋመው ኃውልት እንዲወገድ መጣር የሚሉ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንዔል ጆቴ መስፍንና የኦሃዮ ዩኒቨርሲቲው የፖለቲካ ሣይንስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ብሩክ ኃይሉም በውይይቱ ላይ ተካፍለዋል፡፡

የውይይቱን የመጀመሪያ ክፍል ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ሰማንያኛው የሰማዕታት ቀን
please wait

No media source currently available

0:00 0:25:22 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG