በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የካቲት 12 በቀዝቃዛ ሁኔታ ታሰበ


የካቲት 12 የሰማዕታት አደባባይና መታሰቢያ ኃውልት
የካቲት 12 የሰማዕታት አደባባይና መታሰቢያ ኃውልት

ኢትዮጵያዊያን በፋሽስት ግራዚያኒ የተጨፈጨፉበት ሰባ ሰባተኛ ዓመት ዕለት የካቲት 12 ዛሬ ታስቦ የዋለው እጅግ ቀዝቃዛ በሆነና ጭር ባለ ሁኔታ እንደነበረ ተገለፀ፡፡
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:01 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ኢትዮጵያዊያን በፋሽስት ግራዚያኒ የተጨፈጨፉበት ሰባ ሰባተኛ ዓመት ዕለት የካቲት 12 ዛሬ ታስቦ የዋለው እጅግ ቀዝቃዛ በሆነና ጭር ባለ ሁኔታ እንደነበረ ተገለፀ፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ተባባሪ ንጉሤ አክሊሉ ከአዲስ አበባ ለቪኦኤ ባጋራው ትውስታው በዓሉ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ-መንግሥት በሕገመንግሥት የሠፈረ፤ የአበባ ጉንጉን በሰማዕታቱ ኃውልት ሥር የሚቀመጠው በጠቅላይ ሚኒስትሩ በራሣቸው እንዲሆን የተወሰነበት ዕለት እንደነበረ አንስቷል፡፡

ዛሬ ዕለቱ ሲታሰብ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የፀሎት ሥነ-ሥርዓት መከናወኑን ንጉሤ ጠቅሶ የካቴድራሉም አስተዳዳሪ ዕለቱ ወደፊት የሐይማኖት አባቶችና የአድባራት ሰዎች፣ የዩኒቨርሲቲና በሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እንዲሁም ሌሎችም በተገኙበት ሊታሰብ የሚገባው ዕለት እንደሆነ መናገራቸውን ገልጿል፡፡

ዕለቱን በማስመልከትም የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተሾመ ሙላቱም ንግግር ማድረጋቸው ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር አዲስ የአመራር አባላትን መምረጡንና ፕሬዚዳንቱም የራስ መስፍን ስለሺ የልጅ ልጅ የአርበኛው ዳንኤል መስፍን ስለሺ መሆናቸውንም ንጉሤ አክሊሉ ነግሮናል፡፡

ለተጨማሪ መረጃና የንጉሤ አክሊሉ አስተያየት ከአዲሱ አበበ ጋር ያደረጉትን አጭር ቃለ-ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG