በመሣሪያ የሚፈፀም የጅምላ ግድያ በአሜሪካ እየጨመረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ በአገሪቱ ግዛቶች በመሣሪያ የሚፈፀም ሁከትን መቀነስ ይችሉ ዘንድ፣ የፕሬዝደንት ጆ ባይደን አስተዳደር ተጨማሪ ርዳታ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ነገር ግን፤ የመሣሪያ ሕግን በተመለከተ፣ በአገሪቱ ምክር ቤት ሪፐብሊካን እና ዲሞክራቲክ ፓርቲዎችን ማስማማት አስቸጋሪ ሆኗል።
የቪኦኤዋ ቬሮኒካ ባልዴራስ ኢግሌሲያስ ከክፍፍሉ ጀርባ ያለውን ምክንያት በዚህ የ2023 መጨረሻ ዘገባዋ ተመልክታዋለች፡፡ እንግዱ ወልዴ ወደ ዐማርኛ መልሶታል፡፡
መድረክ / ፎረም