በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ ደቡባዊ ሳዑዲ ዓረብያ የተኮሱት ተወንጫፊ ሚሳይሎች


በኢራን የሚታገዙት የየመኖቹ ታጣቂ ሁቲዎች ወደ ደቡባዊ ሳዑዲ ዓረብያ የተኮሱት ተወንጫፊ ሚሳይል አንድ የውሃ ማጣሪያ ጣቢያ አጠገብ ወድቋል። በሰውም ሆነ በንብረት ላይ ያደረሰው ጉዳት ግን የለም።

ሁቲዎቹን የሚወጋው በሳዑዲ የሚመራው ጦር ሲናገር ሚሳይሉ የወደቀው ጂዛን ክፍለ ሀገር ሹኩዋይክ አካባቢ አቅራቢያ መሆኑን ገልጿል።

የጥምረቱ ቃል አቀባይ ቱርክ አል ማሊኪ በሰጡት መግለጫ “ይህንን ሽብርተኛ ሚሊሽያ ለመመልከት አስቸኳይ ጠንካራ ዕርምጃ እንስወዳለን ብለዋል።

የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ሣራ ሳንደርስ እንዳስታወቁት ስለጥቃቱ ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG