አዳማ —
“የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና ይሰጠን፤ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ” የሚሉ ጥያቄዎችን ይዘው ኦሮምያ ክልል ያቤሎና ሻሸመኔ ከተሞች ውስጥ የተወሰኑ ተማሪዎች ዛሬ ሰልፍ ወጥተዋል።
ያቤሎ ውስጥ ከፖሊስ ጋር በተፈጠረ ግጭት የአንድ ወጣት ህይወት ማለፉና የታሠሩም እንዳሉ ተገልጿል።
ሪፖርተራችን ሙክታር ጀማል ያነጋገራቸው የኦሮምያ ክልል ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እርምጃው ተመጣጣኝ ነበር ብለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡