ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የቻይናውን አቻቸውን ቺ ዪንፒንግን በቤተመንግሥታቸው ተቀብለው ያስተናግዳሉ፡፡
የቻይናው ፕሬዚዳንት የአሜሪካ ጉብኝታቸውን እያደረጉ ያሉት በሁለቱ ሃገሮች መካከል ስፋት ባላቸው አካባቢዎች የግንኙነቶች ውጥረት ባለበት ሁኔታ ነው፡፡
እነዚህ የሥጋት ነጥቦች ከኢንተርኔት ደኅንነት እስከ ቻይና ባሕር መፋጠጥ የተዘረጉ ናቸው፡፡
የቻይናው ፕሬዚዳንት አሜሪካን ለምን በእንዲህ ዓይነቱ የውጥረት ጊዜና ሁኔታ ውስጥ የሚጎበኙት ለምንድነው?
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡