ዋሺንግተን ዲሲ —
በብዙ ሃገሮች ውስጥ ለክሪስማስ ያችን ልዩ የተገለበጠ ዋንጫ ቅርፅ ያላትን የጥድ ዛፍ ማቆም - ማሸብረቅ የተለመደ ነው።
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በየዓማቱ ለገና ከ25 እስከ 30 ሚሊየን የሚደርስ የገና ዛፍ ይሸጣል። ገናም ያልፍና ታዲያ ከዚያ ዛፍ የበዛው ተጠራርጎ ከሚጣል ቀሻሻ ይጣፋል።
የተወሰነው ግን ጥቅም ላይ እንዲውል ይደረጋል። ለጓሮ እርሻ ማዳበሪያ፣ ለመንገድ ዳርና ዳር ተክሎች እግር ማለስለሻ፣ በዝናብ ውኃ መታጠብን መከላከያ እንዲሆን ይፈጫል።
የተወሰነው ደግሞ ለአሦች ሰው ሠራሽ ምቾች ለመስጠት በኃይቆችና በባሕር ዳርቻዎች ላይና በውኃውም ውስጥ እንዲቀመጡ ይደረጋሉ።
የተመረጡት ዛፎች ግን ሃቢታት የሚባለው ግብረሰናይ ድርጅት ለሚቀልሳቸው ቤቶች ግንባታ ግብዓትነት እንዲውሉ ይደረጋል።
ሙሉውን ታሪክ፣ እንዲሁም በዩናይትድ ስቴትስ የተለያዩ የዓለም ዘሪያ ተሰባስበው የሚኖሩ የተለያዩ ባሕሎች አባላት የሆኑ ሰዎች እንዲሁም ዘመናዊዎቹ ሙዚቀኞችና ድምፃዊያን የሚያንቆረቁሯቸውን ጣዕመ-ዜማ የያዘውን የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ