በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመላው ዓለም የኮምፒውተር ሥርዓት ለሠዓታት ተቋረጠ


ተሳፋሪዎች በዶን ሙኢንግ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለመፈተሽ ተሰልፈዋል፤ በባንኮክ፣ ታይላንድ
ተሳፋሪዎች በዶን ሙኢንግ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለመፈተሽ ተሰልፈዋል፤ በባንኮክ፣ ታይላንድ

በመላው ዓለም ዛሬ በኮምፒውተር ሥርዓት ላይ የተፈጠረው እክል ባንኮችን፣ አየር መንገዶችን፣ የሚዲያ ተቋማትንና ሌሎችንም ኩባንያዎችን አስተጓጉሉ ውሏል።

በዓለም ከተከሰቱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መቋረጦች አንዱ ነው ተብሏል።

በመላው ዓለም በርካታ ድርጅቶች የሚጠቀሙት ክራውድስትራይክ የተሠኘ የኮምፒውተር ደህንነት ኩባንያ የላከው የሳይበር ደህንነት ማሻሻያ (አፕዴት) በራሱ እክል የነበረው በመሆኑ የተጠቃሚ ኩባንያዎችን የኮምፒውተር ሥርዓት እንደ ማይክሮሶፍት ያሉ መተግበሪያዎችን እንዳይሠሩ አድርጓል።

ችግሩ ወዲያውኑ መፍትሄ የተበጀለት ቢሆንም፣ የተጠቃሚ ድርጅቶችን ኮምፒውተሮች መልሶ ወደ ሥራ ለማስገባት ሰዓታትን ሊፈጅ እንደሚችል የመስኩ ባለሙያዎች ተናግረዋል።

በርካታ አየር መንገዶች የኮምፒውተር ሥርዓታቸው ባለመሥራቱ መንገደኞች ተስተጓጉለዋል።

ችግሩ ተለይቶ መፍትሄውም ለተጠቃሚዎች እንደተላከ የክራውድስትራይክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጆርጅ ኩርትዝ በማኅበራዊ ሚዲያ አስታውቀዋል።

በችግሩ ምክንያት የክራውድስትራይክ የአክሲዮን ድርሻ ሽያጭ 20 በመቶ ቀንሷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG